ዋጋ ጠይቅ
ፕሮጀክቶችን ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑት ክህሎቶች እና ሞያ አለን
ማሰራት ስለሚፈልጉት ስራ መነጋገር እንፈልጋለን፡፡ አብረን እንስራ፡፡
በስልክ፣ በኢሜይል ወይም ድረ ገጻችን ላይ ያለውን ቅጽ በመሙላት ሊያነጋግሩን ይችላሉ! የሥራ ቡድናችን በተቻለ መጠን በቶሎ ምላሽ ሊሰጥዎት እና የላቁ መፍትሔዎችን ሊሰጥዎት በጉጉት ይጠብቅዎታል፡፡
ቀጠሮ ለማስያዝ የሚፈልጉ ከሆነ የሚመችዎትን ቀንና ሠዓት እንዲያሳውቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ እናመሰግናለን!
የጽሁፍ ትርጉም ማለት አንድን ጽሁፍ ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ የመቀየር ሂደት ነው፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ በትክክል መተርጎምን የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ ለማዘጋጀት ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ የቃል ትርጉም ማለት ደግሞ አንድን ንግግር እዚያው በዚያው ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ የመቀየር ሂደት ነው፡፡ እጅግ የላቀ የማዳመጥ እና የመናገር ክህሎቶችን እንዲሁም ፈጣን እና የሰላ የማሰብ ችሎታን ይጠይቃል፡፡
ለትርጉም አገልግሎት የሚከፈለው ክፍያ ቋንቋዎቹን፣ ርዕሰ ጉዳዩን፣ የማስረከቢያ ጊዜውን እና የሚተረጎመውን ሰነድ ወይም ጽሁፍ ብዛት ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ሊለያይ ይችላል፡፡ ተስፋ የትርጉም እና የቋንቋ አገልግሎት በአጠቃላይ ሁል ጊዜም እጅግ በተሻለ ዋጋ አገልግሎት ሊሰጥዎት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
ለተርጓሚው ግልጽ መመሪያ እና እንደ የቃላት ዝርዝሮችን፣ የዘይቤ መመሪያዎች እና አስቀድመው የተሰሩ ትርጉሞች ያሉ ጠቃሚ የሆኑ የማጣቀሻ ማቴሪያሎችን መስጠትን ጨምሮ ትርጉም ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ማድረግ የሚችሏቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ ትርጉሙን ከተቀበሉ በኋላ ከማናቸውም በጥንቃቄ በማንበብ ከማንኛውም ስህተት የጸዳ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡ ትርጉሙ የተጻፈበትን ቋንቋ በደንብ መናገር የማይችሉ ከሆነ በዚያ ቋንቋ አፉን የፈታ ሰው ትርጉሙን በማንበብ ቢፈትሽልዎት የተሻለ ይሆናል፡፡
ከፍተኛ የትርጉም ጥራት ማረጋገጫ (high-quality translation assurance) ማለት አንድ ትርጉም ከፍተኛ የትክክለኛነት፣ ወጥነት እና ለንባብ ተስማሚነት ደረጃዎችን ማሟላቱ የሚረጋገጥበት ሂደት ነው፡፡ ይህም ምልመላን፣ መተርጎምን፣ አርትኦትን፣ በማንበብ መፈተሽን እና ጥራትን ማረጋገጥን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን ያካትታል፡፡
ትርጉሞች በተቻለ መጠን የላቀ ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተስፋ የትርጉም እና የቋንቋ አገልግሎት የሚያደርጋቸው የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ ብቃት እና ልምድ አለን፣ እያንዳንዱን ትርጉም በሁለተኛ ተርጓሚ እናስገመግማለን፣ የጥራት ማረጋገጫ (quality assurance) ሂደትን እንጠቀማለን፣ ለእያንዳንዱ ነገር ትኩረት እንሰጣለን፣ ባህልን እናስተውላለን እንዲሁም አዲስ ነገር በመማር ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘቡ ትርጉሞችን ለመስራት ዝግጁ ነን፡፡
አንድን ትርጉም ለማጠናቀቅ የሚፈጀው ጊዜ የጽሁፉን ርዝመት እና ውስብስብነት፣ ቋንቋዎቹን፣ ርዕሰ ጉዳዩን እና የማስረከቢያ ጊዜውን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ የሚወሰን ነው፡፡ በጥቅሉ ግን አንድ ተርጓሚ በቀን ከ2,000 እስከ 3,000 ቃላት ይተረጉማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዮች መሰረት በማድረግ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
የተለመዱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው
የጽሁፍ እና የቃል ትርጉም አገልግሎቶችን በተመለከተ ከደንበኞቻችን የሚቀርቡልንን በጣም የተለመዱ ጥያቄዎች በማሰባሰብ የሚከተሉትን እጥር ምጥን ያሉ መልሶች አቅርበናል፡፡ “በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች” በሚለው የድረገጻችን ክፍል ውስጥ የትርጉም አገልግሎቶችን፣ ሂደቶችን፣ የጊዜ ሰንጠረዦችን፣ የሥራ ጥራት አለካክን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡
Tesfa Translation & Lingual Services
ተስፋ የትርጉም እና የቋንቋ አገልግሎት
በኢትዮጵያ እዲሁም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው፣ ዋጋቸው ተመጣጣኝ እና ፈጣን የትርጉም አገልግሎቶችን የሚሰጥ የትርጉም ሥራ ድርጅት፡፡