ከፍተኛ ጥራት ያለው ትርጉም
We make sure your expectations have met.
ከፍተኛ የትርጉም ጥራት ማረጋገጫ
ከፍተኛ የትርጉም ጥራት ለማረጋገጥ አንድ ትርጉም ከፍተኛ የትክክለኛነት፣ ወጥነት እና ለንባብ ተስማሚነት ደረጃዎችን ማሟላቱ የሚረጋገጥበት ሂደት እንከተላለን፡፡
የሚተረጎመው ጽሁፍ በሚመለከተው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ እውቀት ያላቸው እንዲሁም ብቃት እና ልምድ ያላቸው ተርጓሚዎችን መቅጠር፡፡
የትርጉም ሜሞሪ ሲስተምን (translation memory system) በመጠቀም ወጥነትን እና ተክክለኛነትን ማረጋገጥ እና አስቀድመው የተሰሩ ትርጉሞችን እንደ ግብዓት መጠቀም፡፡
የመጀመሪው ጽሁፍ እንዲሁም ትርጉሙ የተጻፈበትን ቋንቋ አቀላጥፎ የሚችል ሁለተኛ ተርጓሚ ትርጉሙን እንዲያርመው ማድረግ፡፡
ትርጉሙን ሦስተኛ ሰው በማንበብ እንዲፈትሸው ማድረግ፤ ይህ ሦስተኛ ሰውም ትርጉሙ በተጻፈበት ቋንቋ አፉን የፈታ ቢሆን ይመረጣል፡፡
የጥራት ማረጋገጫ ሂደትን በመጠቀም ትርጉሙ ትክክል፣ ወጥነት ያለው፣ ለንባብ ተስማሚ እና ባህልን ያገናዘበ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
ትርጉም ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

ግልጽ መመሪያዎችን መስጠት
ታላሚ እንደተደረገው አንባቢ፣ እንደ አገላለጽ ዘይቤ እና እንደ የስታይል መመሪያ ያሉ ከትርጉሙ የሚጠብቋቸውን ነገሮች ለትርጉም አገልግሎት ሰጪው በሚገባ ያሳውቁ፡፡

የማጣቀሻ ማቴሪያሎችን መስጠት
የሚቻል ከሆነ እንደ የቃላት ዝርዝር፣ የስታይል መመሪያ ወይም አስቀድመው የተሰሩ ትርጉሞች ያሉ ማናቸውንም ማጣቀሻ ማቴሪያሎች ለትርጉም አገልግሎት ሰጪው ይስጡ፡፡

ትርጉሙን በማንበብ መፈተሽ
ትርጉሙን ከተረከቡ በኋላ በሚገባ በማንበብ ስህተቶች እንዳሉበት ይፈትሹ፡፡ ትርጉሙ የተጻፈበትን ቋንቋ በደንብ የማይችሉ ከሆነ በዚያ ቋንቋ አፉን የፈታ ሰው ትርጉሙን በማንበብ እንዲፈትሽልዎት ቢያደርጉ ሊሻል ይችላል፡፡
Tesfa Translation & Lingual Services
ተስፋ የትርጉም እና የቋንቋ አገልግሎት
በኢትዮጵያ እዲሁም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው፣ ዋጋቸው ተመጣጣኝ እና ፈጣን የትርጉም አገልግሎቶችን የሚሰጥ የትርጉም ሥራ ድርጅት፡፡