ስለ እኛ
እኛ ማን ነን?
ለቋንቋ ትርጉም ጥያቄዎችዎ ምላሽ እንሰጥዎታለን፡፡
ተስፋ የትርጉም እና የቋንቋ አገልግሎት በኢትዮጵያ እዲሁም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው፣ ዋጋቸው ተመጣጣኝ እና ፈጣን የትርጉም አገልግሎቶችን ለመስጠት በ2007 ዓ.ም. የተቋቋመ የትርጉም ሥራ ድርጅት ነው፡፡
እኛን ተመራጭ የሚያደርገን ምንድን ነው?
በርካታ የተለያዩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የትርጉም አገልግሎቶች

ልምድ እና ብቃት ያላቸው ተርጓሚዎች
ተርጓሚዎቻችን በሚተረጉሟቸው ቋንቋዎች አፋቸውን የፈቱ እንዲሁም በስራው ልምድ እና ብቃት ያላቸው ናቸው፡፡

የተለያዩ የትርጉም አገልግሎቶች
የሰነድ ትርጉምን፣ የቃል ትርጉምን፣ የድረገጽ ትርጉምን እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ጨምሮ የተለያዩ የትርጉም አገልግሎቶችን እንሰጣለን፡፡

ከፍተኛ ጥራት ያለው ትርጉም
ከስህተት የጸዱ፣ ቀልጣፋ እና ባህልን ያገናዘቡ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የትርጉም አገልግሎቶችን ለመስጠት በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡

ዋጋው ተመጣጣኝ እና ቀልጣፋ
አገልግሎታችን ዋጋው ተመጣጣኝ እና ፈጣን ነው፡፡

የደንበኛ እርካታ
ደንበኞቻችንን ለማርካት በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡
ራዕያችን
ራዕያችን የቋንቋን ኃይል በመጠቀም ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከመስተጋብር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን አስወግደው ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ማገዝ ነው፡፡
ተልዕኮአችን
የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ወስነን እንንቀሳቀሳለን፡፡
በዓለም ዙሪያ ላሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው እና ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የትርጉም አገልግሎቶችን መስጠት፡፡
ደንበኞቻችን በማንኛውም ቋንቋ ውጤታማ በሆነ መልኩ ከደንበኞቻቸው፣ ከአጋሮቻቸው እና ከሠራተኞቻቸው ጋር እንዲግባቡ ማገዝ፡፡
በጥራት እና በደንበኛ ግንኙነት አርአያ በመሆን የትርጉም ኢንዱስትሪውን በቁንጮነት መምራት፡፡
እሴቶቻችን
አንኳር እሴቶቻችን ጥራት ያላቸው አገልግሎቶችን እንድንሰጥ እና ጠንካራ የሥራ ቡድን እንዲኖረን የሚያስችሉን ናቸው፡፡

ጥራት
ከስህተት የጸዱ፣ ቀልጣፋ እና ባህልን ያገናዘቡ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የትርጉም አገልግሎቶችን ለመስጠት በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡

የደንበኛ አገልግሎት
ከመጀመሪያው ምክክር አንስቶ ስራውን አስረክበን እስከምናጠናቅቅ ድረስ ለደንበኞቻችን የላቀ የደንበኛ አገልግሎት ለመስጠት ተግተን እንሰራለን፡፡

ዘመናዊ አሰራር
ሁል ጊዜም አገልግሎቶቻንን የምናሻሽልባቸው አዳዲስ መንገዶችን እንፈልጋለን እንዲሁም ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡

ታማኝነት
ከደንበኞቻችን ጋር ባሉን ግንኙነቶች ታማኝ እና ግልጽ ነን እንዲሁም ሁል ጊዜም የምንቀሳቀሰው ሞያን በተላበሰ መልኩ ነው፡፡
ፈጣን ምላሽ እንሰጥዎታለን!
ዋጋ ጠይቅ
የሰነድ ትርጉምን፣ የድረገጽ ትርጉምን፣ የሶፍትዌር ትርጉምን እና የቃል ትርጉምን ጨምሮ ለማንኛውም የትርጉም አገልግሎት የምናስከፍለውን ዋጋ በነጻ ማወቅ ይችላሉ፡፡
Tesfa Translation & Lingual Services
ተስፋ የትርጉም እና የቋንቋ አገልግሎት
በኢትዮጵያ እዲሁም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የንግድ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው፣ ዋጋቸው ተመጣጣኝ እና ፈጣን የትርጉም አገልግሎቶችን የሚሰጥ የትርጉም ሥራ ድርጅት፡፡